በአብክመ የቴ/ሙ/ት/ሥ ፍላጎት ትንበያ (2002-2012)
1. መግቢያ፡-
የአንድን ሀገር የትም/ት ሥርዓት ለሀገሪቱ ዕድገት ከሚያስፈልገው የሠለጠነ የሰው ሀይል ጋር የተመጣጠነ አድርጎ ማቀድና መምራት ለዚህም የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታ በመተንተን ወደፊት ሊኖር የሚችለውን የሥራ እድልና በአጠቃላይም በሥራ ገበያው የሚፈለገውን የሠለጠነ የሠው ሀይል ዓይነትና ብዛት በመለየት ከዚሁ ጋር የሚጣጣም የትም/ትና ሥልጠና አቅርቦት ማቻቸት ለትም/ት ሥርዓቱ ውጤታማነት ወሳኝ ነው፡፡
በተለይም ደግሞ የቴ/ሙ/ት/ሥ ከሥራ ገበያውና ከሚፈለገው የሠለጠነ የሠው ሐይል ጋር ከአለው ቀጥተኛ ተዛምዶ ጋር በተያያዘ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት አቅጣጫ ወደፊት በየትኛው ሴክተር ምን ያህልና ምን ዓይነት የሰራተኛ ሀይል እንደሚፈልግና ከታች ወደ ቴ/ሙ ስልጠና የሚመጣውን የሠልጣኝ ቁጥር ያገናዘበ ዕቅድ ማውጣት ለቴ/ሙ ሥርዓታችን ውጤታማነት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡
በመሆኑም በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት በክልላችን ከ2ኛ ደረጃ 1ኛሳይክልና ከታች ከተለያዩ የክፍል ደረጃዎች ወደ ቴ/ሙ ሊመጣ የሚችለውን የሠልጣኝ ብዛት ከወዲሁ በመለየት ለዚሁ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ለመገኘት በክልላችን በቴ/ሙ/ት/ሥ ከ2002-2012 ዓ.ም ሊኖር የሚችለውን የሠልጣኝ ብዛትና ሊኖር የሚገባው የአሠልጣኝ ቁጥር በዚህ ፕሮጀክት/ትንበያ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
2. አስፈላጊነት፡-
ይህ ትንበያ በክልሉ በመንግስት ቴ/ሙ/ት/ሥ ተቋማትና ኮሌጆች የሚሰጡ ስልጠናዎችን ከክልሉ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎትና ከሥራ ገበያው ጋር የተጣጣመ ለማድረግና ወደፊት በታችኛው የትም/ት እርከን ሊኖር የሚችለውን የተማሪ ቁጥር ያገናዘበ የቅበላ ፣የሠው ሀይል ፣የቁሳዊና የበጀት ዕቅድ በማውጣት ቅድመ ዝግጅቶችን ለማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው፡፡
3. ጠቀሜታ፡-
በክልላችን በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት (2002-2012 ዓ.ም) በመንግስት በኩል ሊኖር የሚችለውን የሥልጠና አቅርቦት ለመለየትና ለዚሁ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ሊገጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ ያስችላል ፡፡ (click to download for more details...)
|