TVET Logo
Home | Statistics | Publications | TVET Institutions| Comments | Contacts
 
 

Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

   

Labor Market Assessment Unit

በሥራ ገበያ ፍላጎት ያልተመራ ሥልጠና  ለሥልጠና የሚወጣውን ወጭ ለብክነት ከመዳረጉም በላይ  ሠልጣኞች ከሥልጠና በኋላ ወደ ሥራ ለመሠማራት ያላቸውን ዕድል በማጥበብ የሠለጠነ የቴ/ሙ ሥራ አጥ በማፍራት በግለሠብም ሆነ በማህበረሠብ ደረጃ የስነ ልቦናና ኢኮኖሚያዊ ጫና ይፈጥራል።በመሆኑም ቴ/ሙ በግለሠብም ሆነ በሀገር ደረጃ ሊያበረክት የሚችለውን ጠቀሜታ መሥጠቱ ቀርቶ በተቃራኒው ያለንን ውስን ሀብት ለብክነት፡ ሠልጣኞችን ለሥራ አጥነት ከዚህም በላይ ደግሞ ማህበረሠቡ በቴ/ሙ/ት/ሥ ያለውን አመለካከት የተዛባ በማድረግ  የሚያሣደረው ጫና ቀላል አይደለም።ከዚህ እውነታ በመነሳት በመተግበር ላይ ባለው አዲሱ የቴ/ሙ/ት/ሥ  ስትራቴጅ መርሆዎች ላይ በግልፅ እንደተቀመጠው  የቴ/ሙ ሥልጠና በሥራ ገበያው ፍላጎት/በኢንዱስትሪው ፍላጎት መመራት ይኖርበታል። ስለሆነም በምናካሂደው የቴ/ሙ የሥልጠና ሂደት ከምንም ሥራችን በፊት በክልል ደረጃ ኤጀንሲው እንዲሁም እያንዳንዱ ኮሌጅና ተቋም የአካባቢውን የሥራ ገበያ/ የቴ/ሙ ዋንኛ ደንበኛ የሆነውን የኢንዱስትሪውን ፍላጎት መለየት ቅድሚያ መሠራት ያለበት ሥራ ነው።
በዘመናችን ባለው ግሎባላይዜሽን ምክኒያት በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚመረቱ ምርቶችና በምርቱ ሂደት ከሚሠማሩ ባለሙያዎች የሚፈለገው ዕውቀትና ክህሎት ተመሳሳይ እየሆነ መጥቷል።በመሆኑም ሰዎች (የሠለጠነ የሠው ሀይል ) ደንበር ሳይገድባቸው ከሚኖሩበት አካባቢና ሀገር በመውጣት ባላቸው ዕውቀትና ክህሎት ወደሥራ ዓለም ሲሰማሩ ይታያል ። ከዚህ ተጨባጭ ዕውነታ በመነሳት  በፌደራልና በክልላችን የቴ/ሙ ስትራቴጂ ራዕይ  ላይ እንደተቀመጠው በቴ/ሙ/ት/ሥ  የሚያልፈው ሀይል በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ይጠበቃል።    (click to download full document)


Labor Market 2003 - 2004

ሥ/ማ/ኤጀንሲ ሥር ባሉ ኮሌጆችና ተቋማት በስፋት በመሰጠት ላይ ያሉትንም ሆነ ወደፊት የሚሰጡትን ስልጠናዎች በክልሉ ከአለው የሠው ሀይል ፍላጎት ጋር የተጣጣመ ለማድረግ ተፈላጊ የሆኑ ሙያዎችን ዓይነት፣ደረጃና ብዛት መለየት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በመሆኑም በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት (2003 ና 2004 ዓ.ም) በክልላችን በሥራ ገበያው ተፈላጊ የሆኑ ሙያዎችን ለይቶ ለማወቅ ይረዳ ዘንድ ይህ የፅሁፍ መጠይቅ ተዘጋጅቷል፡፡

ስለሆነም በክልላችን በአለው የሥራ ገበያ ወደፊት የሚፈለጉ የሙያ ዓይቶችን በመለየት ለዚሁ የሚሆን የሰው ሀይል በሚፈለገው ዓይነት፣ደረጃ፣ጥራትና ብዛት ማሰልጠን ይቻል ዘንድ እርሰዎ የሚሰጡት መረጃ ከምንም በላይ ወሳኝ በመሆኑ ትክክለኛ መረጃ በመስጠት ትብብር ያደርጉልን ዘንድ በአክብሮት እየጠየቅን መጠይቁን በመሙላት ለሰጡን ጊዜ አስቀድመን ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ (Click to download full document)

   

 

     
 
 
 
 
Related Links for this Page...
 
   
 

 Copyright 2011 ANRS Technical Vocational Bureau. Designed by Adewale Adeniyi-Kie