TVET Logo
Home | Statistics | Publications | TVET Institutions| Comments | Contacts
 
 

Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

   

Gemstone Cutting & Polishing...

በመሆኑም የደንበኞች ችግርና ፍላጎት ማዕከል በማድረግ፡-

  • ሰልጣኞች በስራ ስምሪታቸው ብቁና ተወዳዳሪ የሚያደርግ በተግባር የተደገፈ አቅምን ሊገነባ የሚችል ስልጠና ተከታታይነቱን ጠብቆ እንዲያገኙ ማድረግ፣
  • አለን የምንለውን የከበረ ድንጋይ ዓይነት፣ የጥራት ደረጃ፣የገበያ ተፈላጊነት የለዬ ሥልጠናና የምርት ሥራ እንዲኖር መሥራት፣
  • የገበያ መረጃ አገልግሎት በቅርቡና በቀላሉ ተጠቃሚ ማድረግ፣
  • ሰፊና አስተማማኝ የአገር ውስጥም ሆነ የውጭ ገበያ የሚያስገኝ የተጠናከረ የምርትና  የአገልግሎት ማስተዋወቅ ተግባር ማከናወን፣
  • ምርትና አገልግሎቶችን በሚፈለገው መጠንና ጥራት ሊመረቱና ሊቀናበሩ ያልቻሉበትን ችግሮች ለይቶ ችግሮችን የሚፈታ ጥናት በማካሄድ ምርትና አገልግሎቶች በገበያ ተወዳዳሪ መሆን የሚያስችላቸው አቅም መፍጠር፣
  • የሚመረቱ ምርቶች አስተማማኝ ገበያ እንዲያገኙ የሚያስችል ትስስር እንዲኖራቸው  ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና የንግድ ስምምነት /business  contractual  agreement /እንዲጐለብት በማድረግ በውድድር ላይ የተመሠረተ የገበያ ስርዓት እንዲኖር ማድረግ፣

የሚጠበቅብን በመሆኑ በየደረጃው ካሉ አጋር አከላት ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ ከምን ጊዜውም በላይ የተሳካ ተግባራትን በማከናወን የፕሮጀክት ጽ/ቤቱን ተልዕኮ ለማሳካት መረባረብ ይገባናል፡፡
ስለሆነም በ17 የስልጠና ማዕከላት ስኬታማ ተግባራትን ለማከናወን በስልጠና፣ በስራ ስምሪት እንዲሁም በቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች/ተቋማት በማምረቻ ማሽነሪዎች በማምረት ስራ የተሰማራችሁ ሁሉ የተጣለባችሁን ኃላፊነት በሚፈለገው ወቅትና መጠን በመወጣት የከበረ ድንጋይ ልማት በክልሉ ቀዳሚነቱን እንደምታረጋግጡ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የፀና እምነት አለው፡፡

   

 

     
 
 
 
 
Related Links for this Page...
 
   
 

 Copyright 2011 ANRS Technical Vocational Bureau. Designed by Adewale Adeniyi-Kie